የሥልጠና ሪፖርት
በዩንቨርሲቲው በተለያየ የሥራ ክፍል በማገልገል ላይ ላሉ ሰራተኞች የጥናትና ምርምር ዘዴዎች በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ተሠጠ፡፡
የስልጠና መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቶ የቀረበው በሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ሲሆን በስልጠናውም 17 ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
ግማሽ ቀን የወሠደው የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ባለሙያዎች በተቋሙ ውስጥም ሆነ ከተቋሙ ውጭ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን እንዲያከናዉኑ ለማበረታታት ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎችም፤
- መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳቦችን ለማስታወስ እንዲችሉ ለማድረግ፤
- ተገቢውን ክህሎት ለማስጨበጥ፤
- የጥናትና ምርምር ርዕሶችን እንዲለዩ ለማስቻና
- በሥራ ዘርፋቸው የሚገጥሟቸውን ችግሮች በአግባቡ እንዲወጡ ለማገዝ ነው
Recent Comments