ዩንቨርሲቲው የተለያየ የስራ ክፍል በማገልገል ላይ ላሉ ሰራተኞች ሪከርድ ማኔጅመንት በሚል የተዘጋጀ ስልጠና ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተሠጠ፡፡
የስልጠና መርሐ ግብሩ ተዘጋጅቶ የቀረበው በሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ሲሆን በስልጠናውም 32 በቀጥታ የሚመለከታቸው ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
ግማሽ ቀን የወሰደው የዚህ ስልጠና መርሀ ግብር ዓላማ ሠልጣኞች የሠነዶችን ትርጉምና ጥቅም ተረድተው ለዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ መሳካት ያለውን ሚና/ድርሻ/ እንዲጠቀሙበት መርዳት፣የመረጃ ዑደትን ጠብቆ በየደረጃው የሚደረገውን የጥንቃቄ ሁኔታ መጠቆም፣ ወጥነት ያለው የማኅደር አደረጃጀትና ሠነዶች አስተዳደር ሥርዓት እንዲከተሉ መርዳት፣ለአጠቃቀም ምቹና ለሥራ ቅልጥፍና አጋዥ አሠራሮችን መጠቆም እና በዘላቂነት መጠበቅ የሚገባቸው ሠነዶች ደኅንነታቸው ተጠብቆ የሚቆዩበትን ሥልት መጠቆም ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
Recent Comments